Fana: At a Speed of Life!

በከተሞች ዘመኑን የዋጀ የንጹሕ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንዲኖር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በከተሞች ዘመኑን የዋጀ የንጹሕ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንዲኖር በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፡፡

የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ውሃ ቢሮዎች እንዲሁም የከተሞች ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት አመራሮች የንጹሕ መጠጥ ውሃን ይበልጥ ተደራሽ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከሩ ነው፡፡

በሚኒስቴሩ የመጠጥ ውሃ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታምሩ ገደፋ በዚህ ወቅት ÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ ከተሞች አሰራርን ይበልጥ በማዘመን ለደንበኞች ምቹና ቀልጣፋ የውሃ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የንጹህ መጠጥ ውሃን ባልተቆራረጠ መልኩ በከተሞች ተደራሽ ለማድረግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ ከተሞች ውሃና ሳኒቴሽን ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር አህመድ ናቸው።

በዚህ ረገድ የአዲስ አበባ እና አዳማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች ለሌሎች አረአያ የሚሆኑ ሥራዎች መስራታቸውን አንስተዋል፡፡

በቀጣይ በከተሞች የሚስተዋለውን የውሃ አገልግሎት መቆራረጥ በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚሰራም አመልክተዋል፡፡

በጎህ ንጉሱ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.