ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሙዚቃ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ለጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ድጋፍ አድርጓል።
በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አዶኒያስ ወልደ አረጋይ በርክክቡ ወቅት እንዳሉት፤ ትውልድን ለመገንባት እና ትውልድ እንዲገለገልበት በማሰብ ድጋፉ ተደርጓል።
ፋና ሀገራዊ ተቋም እንደመሆኑ የተለያዩ ለሀገር የሚጠቅሙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስታውሰው የዛሬው ድጋፍም የዚህ ተልዕኮ አንድ አካል ነው ብለዋል።
እንዲሁም ፋና በተሰማራበት የሚዲያ ዘርፍ የተለያዩ ለትውልድ የሚጠቅሙ ስራዎችን በመስራት እንደሚገኝ እና እንደዚህ ያሉ ድጋፎችን ማድረጉንም እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ስለተደረገላቸው የሙዚቃ መሳሪያ ድጋፍ አመሰግነዋል።
ኮርፖሬሽኑ በዛሬው ዕለት ካበረከታቸው የሙዚቃ መሳሪያዎች መካከል ፒያኖ፣ ጊታር፣ ክራር እና ስፒከር የመሳሰሉ የሙዚቃ መሳሪያዎች እንደሚገኙበት ተጠቅሷል።
በወንድማገኝ ጸጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!