ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ
በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም በሲዳማ ቡናና ወላይታ ዲቻ መካከል የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ የእግር ኳስ ውድድር መካሄዱ ይታወሳል፡፡
ሁለቱን ክለቦች ለመደገፍ ከሀዋሳ፣ ከወላይታ ሶዶ እና ከአካባቢው የመጡ በርካታ ደጋፊዎች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ ጨዋታው በዝግ ስታዲየም እንዲካሄድ ተደርጎ ፖሊስ በደጋፊዎች መካከል ይፈጠር የነበረውን ግጭት በማስቀረት አስፈላጊውን ወቅታዊና ሕጋዊ ተግባር በመፈፀም ሕግና ሥርዓት አስከብሯል፡፡
ነገር ግን የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት የሚመራቸው በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ያሉ አካላት ተናበው የሰዎች ሕይወት እንዳለፈ አስመስለው በመዘገብ ግጭት ለማባባስ እየሞከሩ እንደሆነ ታዝበናል፡፡
ፖሊስ ግጭቱን ለማባባስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ውስን ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ ሲሆን ውጤቱንም በየጊዜው ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል። ከዚህ ውጭ በአንድም ሆነ በሌላው መልኩ የእርስ በርስ ግጭት የሚፈልጉ አካላት ሰው ሞቷል እያሉ የሚያሰራጩት ወሬ ሀሰተኛ መሆኑን እና በአንድም ሰው ላይ የሞትም ይሁን የአካል መጉደል ጉዳት ያልደረሰ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
ስፖርት በባህሪው የተጣላን የሚያቀራርብ ሆኖ ሳለ በሁለቱ ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ሌላ እንዳይሰፋ ፖሊስ በወሰደው ህጋዊ እርምጃ ግጭቱን ተቆጣጥሯል፡፡
ይሁን እንጂ በሀሰተኛ ወሬ ሕብረተሰቡን ወደ ግጭት እንዲያመራ እና የሕዝብ አለኝታና ጠባቂ የሆነውን ፖሊስ ስም ለማጉደፍ በሚንቀሳቀሱት ላይ ፖሊስ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድና በቀጣይም ስፖርቱ ለእንዲህ ዓይነት ሥርዓት አልበኝነት ተገዢ እንዳይሆን ፖሊስ ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ ያስታውቃል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
ሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን