በኦሮሚያ ክልል ከ27 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች ተጠናቀቁ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዘንድሮ በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል ከ27 ሺህ በላይ አዲስና ነባር ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀዋል አለ የክልሉ መንግሥት፡፡
ለፕሮጀክቶቹ ከ200 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አወሉ አብዲ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
በመንግሥት፣ በሕብረተሰብ ተሳትፎና በአጋር አካላት ትብብር ፕሮጀክቶቹ መጠናቀቃቸውንም ገልፀዋል፡፡
በዚህም ከ45 ሚሊየን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ በሁለት ዙር እንደሚመረቁ ጠቁመው፤ ከዚህ ሣምንት ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 የመጀመሪያው ዙር እንዲሁም እስከ ሐምሌ አጋማሽ 2ኛው ዙር ምረቃ ተከናውኖ አገልግሎት እንደሚጀምሩ አብራርተዋል፡፡
በመራኦል ከድር