Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ2 ሚሊየን በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 2 ሚሊየን 409 ሺህ 196 የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

የክልሉ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተያዘው ወር አጋማሽ እንደሚጀመር ገልጸው÷ የባለፈውን ዓመት አፈፃፀም መነሻ በማድረግ ታቅዶ በ14 ዘርፎች ወደ ተግባር ለመግባት ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ 660 ሺህ ወጣቶችን እንዲሁም ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ 323 ሺህ ሴቶችን በልዩ ሁኔታ ለማሳተፍ መታቀዱን ገልጸዋል።

በበጎ ፈቃድ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የአቅመ ደካሞች የቤት ግንባታና እድሳት በልዩ ትኩረት እንደሚከናወን ጠቁመው÷ በዚህም 600 አዲስ ቤቶችና ከ410 በላይ ነባር ቤቶችን የማደስ ሥራ እንደሚሰራ ለአብነት አንስተዋል።

በአገልግሎቱ ከዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው የሚመለሱ ተማሪዎችን ጨምሮ በየአካባቢው ያሉ ወጣቶች እንዲሳተፉ የሚደረግ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዚህም ወጣቶቹ በሚፈልጉት የሥራ ዘርፍ እንዲሳተፉ ለማድረግ የልየታ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በሚከናወኑ ተግባራት ከመንግስትና ኅብረተሰብ ሊወጣ የሚችለውን 980 ሚሊየን 236 ሺህ ብር ለማዳን መታቀዱን ገልጸዋል።

በመርሐ ግብሩ የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራዎች በግብርና ዘርፍ ተካቶ እንደሚከናወን አንስተው÷ ኅብረተሰቡ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ግንዛቤ የመፍጠር ሥራዎች እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና ላይ የክልሉን ወጣቶች ተሳትፎ ለማሳደግ ግንዛቤ በመፍጠር ስልጠናውን በመውሰድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚሰጥ አብራርተዋል።

ወጣቶች በበጎ ፈቃደኝነት ተሳትፈው ማኅበረሰቡን እንዲያገለግሉ በማድረግ ውጤታማ ሥራ እንዲሰራ ሁሉም አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ኃላፊዋ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.