Fana: At a Speed of Life!

ሰላምና መቻቻል እንዲጎለብት የኃይማኖት ተቋማት የጀመሩትን አስተምህሮ እንዲያጠናክሩ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) “ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለመከባበርና ለአብሮነት” በሚል መሪ ሐሳብ 3ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የሰላም ጉባኤው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሃይማኖት ተቋማት የሀገር ሰላም፣ የህዝብ አንድነት እና ልማት እንዲጠናከር የላቀ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የግጭት መንስኤዎችን በመፍታት ዘላቂ ሰላም እና ልማትን እውን ለማድረግ በውይይት መግባባት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የኃይማኖት ተቋማት የሰላም ጉባኤ በባህርዳር መካሄዱ ልዩ ትርጉም እንዳለው አንስተው÷ በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉን አቀፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ሰላምና መቻቻል እንዲጎለብት፣ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም የህዝብና የመንግስት ግንኙነት የሰመረ እንዲሆን የሃይማኖት ተቋማት የጀመሩትን አስተምህሮ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ዋና ፀሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው÷ ለግጭት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በመነጋገርና በውይይት መፍታት የሁሉም ግደታ መሆኑን አንስተዋል።

በ3ኛ የሃይማኖት ተቋማት የሰላም ጉባኤም በሀገራችን እንዳንድ አካባቢዎች የታዩ ግጭቶችን በመነጋገርና በመመካከር ለመፍታት የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለመምከር መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች እና ከክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በሃይማኖት ተቋማት የተወከሉ የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

የሰላም ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት የሚኖረው ሚና የላቀ ነው ተብሏል፡፡

በደሳለኝ ቢራራ

 

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.