አነስተኛ ማሳ ላላቸው አርሶ አደሮች የፋይናንስና ኢንሹራንስ አገልግሎት እየቀረበ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆኑና በአነስተኛ ማሳ የሚያመርቱ አርሶና አርብቶ አደሮችን የፋይናንስ አቅም በማሳደግ ምርትና ምርታማነታቸው እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ ነው።
በአነስተኛ ማሳ የሚያመርቱ አርሶአደሮች የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትና የፋይናንስ አቅርቦት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት÷ ኢትዮጵያ በ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ለግብርና ዘርፍ በሰጠችው ትኩረት ምርትና ምርታማነትን የበለጠ ማሳደግ መቻሏን አንስተዋል።
በዚህም ሀገራዊ የስንዴ ፍጆታን ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት በመሸፈን ከውጭ የሚገባውን አስቀርተናል ብለዋል።
አካታችና የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መደረጉን ገልጸው÷ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በየዓመቱ የሚተከሉ ችግኞች ሀገሪቱ በምግብ ራስን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።
በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የዜጎችን የአመጋገብ ሥርዓት በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ነው የገለጹት።
በአነስተኛ ማሳ የሚያመርቱ አርሶና አርብቶ አደሮች ለአየር ንብረት ለውጥ የበለጠ ተጋላጭ መሆናቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያ ተፅዕኖውን ለመቋቋም አሰራር መዘርጋቷን ገልጸዋል።
የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲው አነስተኛ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮች በቀላሉ የፋይናንስ ብድር አቅርቦት እንዲያገኙ ዕድል መስጠቱን አመልክተዋል።
በዚህም ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆኑ አርሶና አርብቶ አደሮች የፋይናንስ እና የኢንሹራንስ አቅማቸውን የበለጠ እንዲያጠናክሩ በማገዝ ምርታማነታቸው እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አካታች የፋይናንስ ሥርዓት በመዘርጋት የገጠር ልማትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!