Fana: At a Speed of Life!

በተሳሳተ ትርክት የተሸረሸሩ ባህሎችን ለማጎልበት እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና መግባባትን በመፍጠር በተሳሳተ ትርክት እየተሸረሸሩ የመጡ ባህልና ዕሴቶችን ለማጎልበት እየተሠራ ነው፡፡

ሰላም ሚኒስቴር ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር “በጎነት ለአብሮነት” በሚል መሪ ሐሳብ ለ13ኛ ጊዜ በብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ስልጠና ያሰለጠናቸውን በጎ ፈቃደኞች አስመርቋል፡፡

ወጣቱ በብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰልጥኖ ሕብረተሰቡን ማገልገል እንዲችል እየተሠራ መሆኑን የሰላም ሚንስትር ዴዔታ አማካሪ ፍሬሰንበት ወልደትንሳኤ ገልፀዋል፡፡

ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና መግባባትን በመፍጠር በተሳሳተ ትርክት እየተሸረሸሩ የመጡ ባህልና ዕሴቶችን ለማጎልበት እየተሠራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አወል ሰዒድ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ለበጎ ፈቃደኞቹ ማኅበረሰቡን እንዴት ማገልገል እንዳለባቸው ከማስተማር ባለፈ በኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰላምና ልማት ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠራቸውን አንስተዋል።

ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ክኅሎት በመጠቀም ሕብረተሰቡን ለማገለግል ቁርጠኛ መሆናቸውን ያረጋገጡት ደግሞ ተመራቂ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ናቸው፡፡

በሰብለ አክሊሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.