Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ላይ በተሰሩ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች እየታዩ ነው – ምሁራን

አዲስአበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በአጋር አካላት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዲያገኝ በተሰሩ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው፡፡

ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ብሔራዊ አጀንዳንቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጎልቶ ወጥቷል ብለዋል።

ጉዳዩን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገራትም በቅርበት እንዲከታተሉት ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ የንግድና አገልግሎት ግብይት ውስጥ ለመግባት የባህር በር ማግኘት ለኢትዮጵያ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕግን መሰረት በማድረግ እያቀረበች ያለው የባህር በር ጥያቄ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እያገኘ መጥቷል ነው ያሉት።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪ ንጋቱ አበበ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ መንግስት ላለፉት ሶስት አስርት አመታት አይነኬ የነበረውን የባህር በር ጥያቄ የህዝብን ፍላጎት መሠረት አድርጎ አንስቷል።

የጉዳዩ ብሔራዊ አጀንዳነትም ከመቼውም ጊዜ በላይ ጎልቶ መውጣቱን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከባህር መራቋ ኢፍትሐዊ እንደሆነ የገለጹት ደግሞ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ እንዳለ ሙላቱ ናቸው።

ኢትዮጵያ በታሪክ በባህር በር ላይ የነበራትን ስም ለማስመለስ ምንም የሚከለክላት ነገር እንደሌለ በማንሳት ዓለም አቀፍ ሕጉ የሚደግፋት መሆኑን አስረድተዋል።

እንደ ምሁራኑ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ዓለም አቀፍ ሕጎችን ማዕከል አድርጎ በመጓዝ ምላሽ የሚያገኝበት ዕድል ከፍተኛ ነው።

የኢትዮጵያ ጥያቄ ተገቢ በመሆኑ አሜሪካን ጨምሮ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገራት ትኩረት እንደሰጡት አንስተዋል።

ወደቦችን እና መሠረተ ልማቶችን በጋራ የማልማት ተሞክሮ መጠቀም፣ የኢትዮጵያ የማደግ ፍላጎት፣ እያደገ ያለውን ህዝብ ብዛት የሚመጥን ኢኮኖሚ ለመገንባት የባህር በር ጥያቄው ምላሽ ማግኘት የሉአላዊነት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

በአስጨናቂ ጉዱ

 

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

 

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.