በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የወባ በሽታ ሥርጭትን ለመቆጣጠር እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መጪውን የክረምት ወራት ተከትሎ የሚከሰተውን የወባ በሽታ ሥርጭት ለመቆጣጠር በትኩረት እየተሰራ ነው።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ባለፉት 10 ወራት 1 ሚሊየን 772 ሺህ 822 ሰዎች የወባ በሽታ ምርመራ ተደርጎላቸዋል።
ከእነዚህ መካከል 1 ሚሊየን 84 ሺህ 311 ሰዎች የወባ በሽታ ተገኝቶባቸው የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸዋል።
በተደረገው ምርመራ በወባ የመያዝ ምጣኔ 61 ነጥብ 1 በመቶ እንደሆነ ጠቅሰው÷ ከፍተኛ የወባ ጫና ባለባቸው ወረዳዎች የቤት ለቤት የወባ መከላከያ ኬሚካል ርጭት መካሄዱን ጠቁመዋል።
የቅኝትና አሰሳ ስራዎችን በማጠናከር የቤት ለቤት ጉብኝት በማካሄድ 1 ሚሊየን 647 ሺህ 379 ቤቶችን በመጎብኘት የአልጋ አጎበር አጠቃቀምና ሌሎች ተያያዥ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች 1 ሚሊየን 247 ሺህ 486 ካሬ ሜትር ቋሚ እና 2 ሚሊየን 614 ሺህ 852 ካሬ ሜትር ጊዜያዊ የወባ ትንኝ መራቢያ ስፍራዎችን የማፋሰስና ማዳፈን ስራዎችም ተሰርተዋል ነው ያሉት።
በዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በሰው ኃይልና በማሸን የማፋሰስና የማዳፈን ተግባራት መከናወኑን አመልክተዋል።
አሁን ላይ የወባ በሽታ ስርጭት የሚጨምርበት ወቅት በመሆኑ 232 ሺህ 222 የአልጋ አጎበር ለኅብረተሰቡ ለማሰራጨት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አቶ ኢብራሂም ገልጸዋል፡፡
የወባ በሽታን ለመከላከል ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየተሰራ መሆኑን አንስተው÷ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ያለመዘናጋት የወባ በሽታ የመከላከል ጥረትን እንዲደግፍ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!