Fana: At a Speed of Life!

5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በዛሬው ዕለት ይጀመራል፡፡

በውድድሩ የምዕራፍ 17፣ 18 እና 19 አሸናፊዎች እንዲሁም ምርጥ አራት ተሰናባቾች ዳግም ተመልሰው በአጠቃላይ 16 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ፡፡

ለአሸናፊዎች አጠቃላይ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን÷ የዋንጫ እና አዲስ ወጥ ሙዚቃ ሽልማትም ተዘጋጅቷል፡፡

የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት በሚያደርገው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖራል፡፡

በ13ኛው ሳምንት አራት ምርጥ ተወዳዳሪዎች ለፍጻሜው የሚፋለሙ ሲሆን÷ 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ኮከብ ይለይበታል።

ውድድሩ በየሳምንቱ በተለያየ ሙያ ውስጥ ባሉ ተጋባዥ ዳኞች ጭምር ይደምቃል።

የመጀመሪያው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ መቅደስ ግርማ ስትሆን÷ አህመድ ሁሴን፣ ያለምወርቅ ጀምበሩ እና ባምላክ ቢያድግልኝ ደግሞ በቅደም ተከተል 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛውን ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለት ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን 6:00 ላይ የሚጀመረው 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ደማቅ ውድድር በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሁሉም አማራጮች በቀጥታ ሥርጭት ይተላለፋል። ይጠብቁን፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.