5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር መካሄድ ጀምሯል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል፡፡
የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው የውድድሩን መጀመር አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፤ እንኳን ለዚህ ልዩ ቀን አደረሳችሁ ብለዋል።
ፋና ላምሮት የዕድል እና የድል መገናኛ መድረክ ነው በማለት ገልጸው፤ የፋና ላምሮት ሂደት ብቃትን፣ መማማርን፣ መደማመጥን ተስፋ አለመቁረጥ እና መቻልን የምንማርበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ፋና ላምሮት ሁልጊዜ ቤተሰቦቹን የሚያዳምጥ መሆኑን በመግለጽ፤ ፋና ላምሮት ከሙዚቃ ውድድርነት ባሻገር ለጥበብ ቤተሰቦች ድልድይ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በድምጽ ውስጥ ምስል፤ በምስል ውስጥ ትውልድ የሚታይበት እንዲሁም የውድድሩ ዳኞች ዕውቀታቸውን የሚያካፍሉበት፣ ተወዳዳሪዎች እና አድማጭ ተመልካቾች ዳኝነት የሚሰጡበት መሆኑን ተናግረዋል።
ፋና ላምሮት ነገን የተሻለ ለማድረግ ጥረት የሚደረግበት የዕውቀት መድረክ ነው ብለዋል።
ፋና ላምሮት ኮከቦችን ማፍራት ብቻ ሳይሆን ተሰጥኦ በየቤቱ መሰረት እንዲይዝ በማድረግ በድል ታጅቦ ለ5ኛው ኮከቦች የደረሰ ፕሮግራም መሆኑን አብራርተዋል።
በውድድሩ የምዕራፍ 17፣ 18 እና 19 አሸናፊዎች እንዲሁም ምርጥ አራት ተሰናባቾች ዳግም ተመልሰው በአጠቃላይ 16 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ፡፡
ለአሸናፊዎች አጠቃላይ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን÷ የዋንጫ እና አዲስ ወጥ ሙዚቃ ሽልማትም ተዘጋጅቷል፡፡
የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት በሚያደርገው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖረዋል።
በ13ኛው ሳምንት አራት ምርጥ ተወዳዳሪዎች ለፍጻሜው የሚፋለሙ ሲሆን÷ 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ኮከብ ይለይበታል።
ውድድሩ በየሳምንቱ በተለያየ ሙያ ውስጥ ባሉ ተጋባዥ ዳኞች ጭምር ይደምቃል።
የመጀመሪያው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ መቅደስ ግርማ ስትሆን÷ አህመድ ሁሴን፣ ያለምወርቅ ጀምበሩ እና ባምላክ ቢያድግልኝ ደግሞ በቅደም ተከተል 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛውን ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
በዛሬው ዕለት ቀን 6:00 ላይ የጀመረው 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ደማቅ ውድድር በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሁሉም አማራጮች በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ ይገኛል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!