ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እየተደረጉ የሚገኙ ውይይቶች መቀጠል አለባቸው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግስት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እያደረገ የሚገኘውን ውይይት ማስቀጠል ይገባል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተለያዩ የሕብረተሰብ ተወካዮች ጋር እያደረጓቸው የሚገኙትን ውይይቶች በተመለከተ ከፋና ፖድካስት ጋር ቆይታ ያደረጉት የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ጥላሁን ሊበን÷ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ችግሮች በንግግር የሚፈቱ በመሆናቸው የሚደረጉ ውይይቶች ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ችግሮችን በንግግር የመፍታት ሀገራዊ እሴት እንዳላት አንስተው÷ ውይይቶቹ የሕዝብ ጥያቄን እና ሃሳብ ለመስማት እንዲሁም መፍትሔ ለመስጠት እንደሚያግዙና ተገቢ ጥናት በማድረግ ችግሮችን መለየት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
አንዱ የመንግስት ኃላፊነት የሕዝብን ድምጽ ማዳመጥ እንደሆነ አንስተው÷ በውይይቶቹ የተነሱ ችግሮች በአንድ ጀንበር መፍትሔ የሚያገኙ እንዳልሆኑና በጊዜ ሂደት ለመፍታት ሁሉም አካላት ሊሰሩ የሚገባቸው እንደሆኑ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር በተለያዩ መንገዶች ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚነካ በመሆኑ የሚፈታውም አንድ በመሆንና ውይይት የችግሮች መፍቻ ቁልፍ ነው ብሎ የሚያምን ትውልድ በመፍጠር እንደሆነ አመላክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮችን እንዳወያዩ እና ይህንን አይነት እንቅስቃሴ በተዋረድ የሚገኙ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ምሁራንን ጨምሮ ሁሉም ዜጋ ሊተግብረው እንደሚገባ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግጭት የተረጋጋ መንግስት እንዳይኖር ማድረጉን አንስተው÷ በጦርነት የሚፈታ የህዝብ ጥያቄ አለመኖሩን አስገንዝበዋል።
ሁሉም ዜጋ ጥያቄ ቢኖረውም ለጥያቄው በአንድ ጀምበር ምላሽ መስጠት እንደማይቻልና በሂደት ለመፍታት መሰራት እንዳለባቸው አጽንዖት ሰጥተዋል።
የተለያዩ ሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየታቸው በራሱ ግብ እንዳልሆነ ያነሱት አቶ ጥላሁን÷ ሁሉም አካላት ችግሮችን ለመፍታት በሚችሉት አቅም ሁሉ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
መንግስት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እያደረገ የሚገኘውን ውይይት ማስቀጠል እና የተነሱ ጥያቄዎችን እንደ ግብዓት በመውሰድ ለመፍትሔት ሊሰራ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!