Fana: At a Speed of Life!

በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው ኤሌክትሪክ ሙሉ ለሙሉ ተመልሷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ ለሙሉ ተመልሷል አለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፡፡

የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዋር አብራር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ ከዋናው ግሪድ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ሳቢያ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ ለሙሉ ተመልሷል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባደረገው ርብርብ ብልሽቱ ተቀርፎ አሁን ላይ አዲስ አበባ ጨምሮ በሁሉም አካባቢዎች አቅርቦቱ ሙሉ በሙሉ መመለሱን አረጋግጠዋል፡፡

ብልሽቱ ተስተካክሎ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ለጠበቁ ደንበኞችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.