የጅግጅጋ የኮሪደር ልማት በቅርቡ ይጠናቀቃል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅግጅጋ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በቅርቡ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል፡፡
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ ÷ የከተማውን የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
አቶ ሙስጠፌ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የእግረኛ መንገድ፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የብስክሌት መንገድና ዘመናዊ የመንገድ ዳር መብራትን ያካተተው የኮሪደር ልማት በጥራት እየተከናወነ ይገኛል።
የኮሪደር ልማቱ የጅግጅጋ ከተማን ለነዋሪዎች ጽዱ እና ምቹ እንድትሆን ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡
ሥራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡
በተስፋዬ ሀይሉ