Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና አንጎላ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና አንጎላ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግና አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላትን ሚና ለማጎልበት ትብብሯቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከአንጎላው ፕሬዚዳንት እና ከወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር ጆ ሎሬንዞ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በአንጎላ ርዕሰ መዲና ሉዋንዳ እየተካሄደ ከሚገኘው የአፍሪካ-አሜሪካ የቢዝነስ ፎረም ጎን ለጎን ነው የተካሄደው፡፡

መሪዎቹ የሀገራቱን ግንኙነትና ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ምቹ ሁኔታ ዙሪያ መምክራቸውን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዘርይሁን አበበ ተናግረዋል፡፡

በተለይም ግንኙነቱን ለማጠናከር ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ከግምት በማስገባት መሪዎቹ ከዚህ ቀደም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተቋቋመው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚቴ በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ መግባባት ላይ ደርሰዋል ብለዋል።

ይህን ተከትሎም በሁለቱም ወገን ያሉ ሚኒስትሮች መመሪያ እንዲሰጣቸው መምከራቸውን ነው ያስረዱት፡፡

ሁለቱ መሪዎች በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በተለይም አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላትን ሚና ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይም ተወያይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.