ዩኒቨርሲቲው ከ7 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ነጻ ሕክምና ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ7 ሺህ 200 ዜጎች የነጻ ምርመራና ሕክምና አገልግሎት ሰጥቻለሁ አለ፡፡
የዩኒቨርሲቲው ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ደስታ ጋልቻ÷ ኮሌጁ በመደበኛና ድንገተኛ ሕክምና ለማሕበረሰቡ ሰፊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።
ኮሌጁ በዘንድሮው ዓመት 150 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ ለ7 ሺህ 200 ዜጎች በተለያዩ ሕክምና ዘርፎች የነጻ ምርመራና ሕክምና አገልግሎት መስጠቱን ነው የገለጹት፡፡
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አብደላ ከማል (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ተቋሙ ከመማር ማስተማር ሥራ ጎን ለጎን የማሕበረሰብ አገልግሎት ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በዚህም ዩኒቨርሲቲው በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ውሰጥ የሚሰጡ ሁለት ፕሮግራሞች በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።
በማቴዎስ ፈለቀ