ዐይነ ስውሯ የስፌት ባለሙያ…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሐና ደበሌ በስምንት ዓመት እድሜዋ በገጠማት ድንገተኛ ሕመም ምክንያት የዐይን ብርሃኗን አጥታለች።
በልጅነቷ ማየት አለመቻሏን አገናዝባ ጉዳቱን መመዘን ባትችልም አሁን ላይ በአቅም ማነስ ምክንያት ከትምህርት እና ከተለያዩ ሥራዎች መስተጓጎሏ ቁጭት ያሳድርባትል፤ ሆኖም ሐና ለሁሉም ነገር እጅ አልሰጠችም።
ሐና በዐይን ሕመሟ ምክንያት በተወለደችበት የገጠር አካባቢ መኖር አስቸጋሪ ስለሆነባት ወደ አዲስ አበባ መጥታ ኑሮዋን ከእህቷ ጋር እንዳደረገች ትናገራለች፡፡
በኋላም ሞያ እያለኝ ሰው አላስቸግርም በማለት ባላት አቅም ቤት ተከራይታ የግል ሕይወቷን ያለ አጋዥ መምራት ትጀምራለች።
በልጅነቷ ከእናቷ እጅ እንደቀልድ የተማረችው ሙያ ዛሬ ላይ የኑሮዋ ምሰሶ ሆኖላት ዐይነ ስውር ሆና ልቅም ያለ የስፌት ሥራ እንድትሰራ አስችሏታል።
የስንደዶውን ቀለም በእጇ በመዳሰስ ብቻ እየለየች ከሰበዟ ጋር በማዋደድ በተለያየ ቀለም ያሸበረቁ ሰፌዶች፣ የዳቦና የእንጀራ መሶቦችን በፍጥነትና በጥራት የምትሰራበት ሁኔታ ለበርካቶች አርአያ የሚሆን ነው፡፡
ሐና የቤት ውስጥ ሥራዋን ሳትደናቀፍ ትከውናለች፤ እንደቤት ማጽዳት፣ ምግብ ማብሰል እና ልብስ ማጠብ ያሉ የቤት ሥራዎችን ለማከናወን የማንንም ድጋፍ አትጠይቅም።
የእጅ ስራ ውጤቶቿን ለሚያዟት ሰዎች ብቻ እንደምትሰራ የምትናገረው ሐና÷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተቀዛቀዘው ገበያዋ ኑሮዋን ቢያከብድባትም ፈተናዎቿን በጽናት እየተሻገረች በተሰጣት ስጦታ ፈጣሪዋን ታመሰግናለች።
ሐና የዐይን ሕመሟ መዳን የሚችል መሆን አለመሆኑን በቂ ሕክምና ባለማድረጓ ምክንያት ማወቅ አለመቻሏን ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራት ቆይታ ተናግራለች፡፡
ለሌሎች የጥንካሬ ምሳሌ መሆንና ከሕመሟ ድና በችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች መድረስ ደግሞ የልበ ብርሃኗ ሐና የምንጊዜም ምኞት ነው።
በበጸሎት መንገሻ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!