Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል – የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኢትዮጵያ በጤና ዘርፍ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል አለ ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው “የሬይስ ኦፍ ሆፕ 2025” ጉባኤ ጎን ለጎን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጨረራ ሕክምና ማዕከልን ጎብኝተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ ወቅት ተቋማቸው ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፥ በቀጣይ በቋሚነት አስፈላጊውን የሕክምና ግብዓት ድጋፍ ለማድረግ ከአጋር አካላት ጋር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
ከሕክምና ግብዓቶች በተጨማሪ የቴክኒክና የስልጠና ድጋፎችን ማድረግ እንደሚቀጥሉም ነው የገለጹት፡፡
ሆስፒታሉ በውስን የካንሰር ሕክምና መሳሪያዎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፥ በቀጣይ የሚስተዋሉ ክፍተቶች በጋራ ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል።
በሆስፒታሉ ዘመናዊ የኒውክለር ሜዲስን ማዕከልን መርቀው ከፍተዋል።
በመራኦል ከድር
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.