በኢትዮጵያ ዲጂታል የገንዘብ ዝውውር 12 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ዲጂታል የገንዘብ ዝውውር 12 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ደርሷል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፥ የፋይናንስ ዘርፍ በዚህ ዓመት አዎንታዊና ጤናማ ዕድገት አስመዝግቧል ብለዋል።
ዲጂታል የገንዘብ ዝውውር 12 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር መድረሱን ገልጸው፥ ከጥሬ ገንዘብ ግብይቱም ከፍተኛ ብልጫ እንዳለው አንስተዋል፡፡
የሞባይን ገንዘብ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 55 ሚሊየን መድረሱን ገልጸው፥ ለ11 ሚሊየን የጥቃቅንና አነስተኛ ተበዳሪዎች 24 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በዲጂታል ብድር አማካኝነት ተደራሽ ሆኗል፡፡
በአጠቃላይ በዓመቱ የታቀደው 8 ነጥብ 4 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚሳካ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በአገልግሎትና ሌሎችም ዘርፎች የተገኙ ውጤቶች አመላካች ናቸው ብለዋል።
በኃይለማርያም ተገኝ