Fana: At a Speed of Life!

በዞኑ በበልግ እርሻ በዘር ከተሸፈነው መሬት 8 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በበልግ እርሻ በዘር ከተሸፈነው 368 ሺህ ሄክታር መሬት 8 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል አለ የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት።

የኦሮሚያ ክልልርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በምዕራብ ጉጂ ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

የስራ ሃላፊዎቼ በምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮ በርጉዳ ወረዳ በክላስተር የለማ ስንዴ እና ጤፍን ጎብኝተዋል።

የምዕራብ ጉጂ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ቱኬ አና ለከፍተኛ የስራ ሀላፊዎቹ በሰጡት ማብራሪያ፤ በዞኑ በተያዘው የክረምት ወራት 368ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ የዘር ዓይነት መሸፈኑን ገልጸዋል።

368ሺህ ሄክታር መሬት በበቆሎ፣ ስንዴ፣ ቦሎቄ፣ ጤፍ፣ ማሾ እና ሌሎች ሰብሎች መሸፈኑን የጠቆሙት ሃላፊው ÷ከዚህም 8 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት  ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የአርሶ አደሩ የሥራ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ምርታማነት እንዲያድግ መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ጠቁመው÷ መንግስት  ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያና ሌሎች ግብዓቶችን አቅርቧል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.