ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር በሀገራቱ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ዛሬ ጠዋት ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር 55 ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ግንኙነታቸው በሁኔታዎች ሁሉ እንደማይቀያየር አጋሮች ባለፉት ሰባት ዓመታት ትብብራችን ጉልህ ፍሬዎችን አፍርቷል በማለት ገልጸዋል።
ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና አይሲቲን ባካተቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዓምዶች ላይ ትኩረታችን እንዳለ ሆኖ ሌሎች የትብብር መስኮችን ለማጠናከርና እንደ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ ሎጂስቲክስ እና ንጹሕ የኃይል ምንጮች ልማት ላይ ያለንን ዕምቅ ዐቅም ለመመልከትም ችለናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!