በግብርና መስክ የተሰማሩ ባለሃብቶች አርሶ አደሩን በቴክኖሎጂ መደገፍ አለባቸው – ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሞድ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል የግብርና ልማትን በማዘመን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የባለሃብቶች ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሞድ።
ርዕሰ መስተዳድሯ በጋምቤላና አበቦ ወረዳዎች ከዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በባለሃብቶች እየለማ የሚገኝን ማሣ ዛሬ በተመለከቱበት ወቅት እንዳሉት፤ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ኢንቨስትመንት የላቀ ድርሻ አለው።
ባለሀብቶች ባሉት ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች በመሰማራት ለክልሉ ልማትና እድገት ተሳትፏቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በተለይም የግብርናውን ልማት በማዘመን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ለተጀመረው ጥረት በግብርና መስክ የተሰማሩ ባለሃብቶች አርሶ አደሩን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ረገድ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ባለሃብቶች በግብርና ላይ ተሰማርተው ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሯ÷ ሌሎች ባለሃብቶችም ወደ ክልሉ በመምጣት በተመሳሳይ ልማት እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሎው ኡቡፕ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በክልሉ አስተማማኝ ሰላም በመፈጠሩ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሰማራት ወደ አካባቢው የሚመጡ ባለሃብቶች ፍሰት ጨምሯል ብለዋል።
በተለይም በግብርና መስክ ፍቃድ የወሰዱ ባለሃብቶች ወደ ልማት በመግባት ውጤታማ ስራዎችን እያከናወኑ እንደሆነ ገልጸው፤ ለባለሃብቶቹ አስፈለጊው ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!