በኢትዮጵያና ኮሞሮስ መካከል ያለው ሁለንተናዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሰራል – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ እና ኮሞሮስ መካከል ያለው ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሰራል አሉ።
ኮሞሮስ ነፃነቷን የተጎናጸፈችበትን 50ኛ ዓመት የነፃነት በዓል ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በድምቀት አክብራለች።
በዓሉን የታደሙት ፕሬዚዳንት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በኮሞሮስ የነፃነት በዓል መሳተፏ በሀገራቱ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ መምጣቱን ያሳያል።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የቆየ ወዳጅነት በማጠናከር አህጉራዊ ትስስርና አንድነት እንዲጎለብት እንደምትሰራም አንስተዋል።
የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በፀረ ቅኝ ግዛት ትግል ሂደት መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።
ከነፃነት በኃላ ባለፋት 50 ዓመታት የተገኙ ለውጦች ሀገሪቱን ወደ ተሻለ የታሪክ ምዕራፍ እንዳሸጋገራት መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በትምህርት፣ በጤና፣ በገቢ፣ በቱሪዝም እና በመሰረተ ልማት ዘርፎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እንደተመዘገቡም ነው የገለጹት።
ኮሞሮስ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣችው በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሰኔ 29 ቀን 1967 ዓ.ም ነው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!