የቢሾፍቱን የኮሪደር ልማት ከሐይቆች ጋር የማስተሳሰሩ ሥራ…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቢሾፍቱ ከተማን የኮሪደር ልማት ሥራ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የከተማ አስተዳደሩ፡፡
የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ የኮሪደር ልማቱ የቢሾፍቱ ከተማን ውብና ጽዱ ከማድረግ ባለፈ የቱሪስት መዳረሻነቷን ያጠናክራል፡፡
ቢሾፍቱ በተፈጥሮ የታደለችና የሰባት ትላልቅ ሐይቆች መገኛ መሆኗን አውስተው ÷ የኮሪደር ልማቱን ከከተማዋ ሐይቆች ጋር ለማስተሳሰርና አገልግሎቱን ለማሳለጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የከተማዋ የኮሪደር ልማት ሥራ 58 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ÷ በሶስት ምዕራፎች ተከፍሎ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
አሁን ላይ የኮሪደር ልማት ሥራው 85 በመቶ ደርሷል ያሉት ምክትል ከንቲባው ÷ በቅርቡ ለማጠናቀቅ በትብብር ይሰራል ነው ያሉት፡፡
በኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ውበት ይበልጥ የሚያጎናጽፉ ሥራዎች በ34 ሄክታር መሬት ላይ መከናወናቸውን አስረድተዋል፡፡
ከእነዚህ መካከልም የአረንጓዴ ሥፍራዎቸ፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ እግረኛ መንገዶች፣ የመዝናኛ እና የመጫወቻ ሥፍራዎች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል፡፡
በሌላ በኩል የከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻነት ይበልጥ ለማስፋት ሐይቆችን ያማከለ የኮንፈረንስ ማዕከል ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱ የአስፋልት መንገድ፣ ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዮች፣ የመንገድ ዳርቻ ማስዋብና የአረንጓዴ ሥፍራዎች እንዲሁም የሳይክልና እና የእግረኛ መንገዶችን እንዳካተተ ጠቁመዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!