ኒውካስል ዩናይትድ አንቶኒ ኤላንጋን ለማስፈረም ተስማማ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኒውካስል ዩናይትድ ስዊድናዊውን የመስመር አጥቂ አንቶኒ ኤላንጋ ከኖቲንግሃም ፎረስት ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡
ኒውካስል ዩናይትድ ለተጫዋቹ ዝውውር 55 ሚሊየን ፓውንድ እንደሚከፍል ተነግሯል፡፡
የ23 ዓመቱ የቀድሞ የማንቼስተር ዩናይትድ ተጫዋች በኒውካስል ዩናይትድ የአምስት አመት ውል እንደሚፈርም ተዘግቧል፡፡
አንቶኒ ኤላንጋ ባለፈው የውድድር አመት ለኖቲንግሃም ፎረስት በሁሉም የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን፥ በሊጉ በ17 ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል፡፡