Fana: At a Speed of Life!

ሠራተኞች ብክነትና ሌብነትን በመከላከል በታማኝነትና በትጋት ሊሰሩ ይገባል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሠራተኞች ብክነት እና ሌብነትን በመከላከል በታማኝነት እና በትጋት ሊሰሩ ይገባል አሉ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ መንገዶች ባለስልጣን ሠራተኞች በ2017 በጀት ዓመት ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት ያመሰገኑ ሲሆን÷ የደረጃ እድገትም ሰጥተዋል፡፡

የባለስልጣኑ ሠራተኞች በ2017 በጀት ዓመት በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ መስክ ላስገኙት ስኬት ነው የምስጋና እና የደረጃ እድገት የተሰጣቸው፡፡

የደረጃ እድገቱ ሠራተኞች ከ2009 ጀምሮ የደሞዝ ማሻሻያ ያልተደረገላቸው መሆኑን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ከንቲባ አዳነች እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት በተካሄደው መርሐ ግብር የመስሪያ ቤቱ ሠራተኞች የደረጃ እድገትና የደሞዝ ማሻሻያ በከተማ አስተዳደሩ ጸድቆ ይፋ ተደርጓል፡፡

ከንቲባዋ በዚህ ወቅት “መስራት ያስከብራል ፤ ውጤት ማስመዝገብም ያሸልማል ሲሉ መናገራቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

ሠራተኞች ብክነትና ሌብነትን በመከላከል በታማኝነት እና በትጋት መዲናዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የተሰጠው እውቅና ይበልጥ በመስራት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያነሳሳ መሆኑን ጠቁመው÷ በቀጣይ ጥራትን በመጨመር፣ ብክነትን በማስወገድና ፍጥነትን በማሳደግ እንዲሰራም መመሪያ ሰጥተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.