Fana: At a Speed of Life!

በሸገር ከተማ በ40 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሸገር ከተማ አስተዳደር በመንግስትና በሕብረተሰቡ ተሳትፎ በ40 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት እየተደረጉ ነው፡፡

የሸገር ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላይ ረጋሳ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የማሕበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በተለይም የመሰረተ ልማት እና የተሳለጠ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግና ለማጠናከር ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

አሁን ላይም በተለያዩ አካባቢዎች በመንግስት እና በሕብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት እየበቁ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የልማት ፕሮጀክቶቹ ከ8 ሺህ 900 በላይ መሆናቸውን ገልጸው÷ ከ40 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም 17 ቢሊየኑ ከመንግስት ወጪ የተደረገ ሲሆን÷ 23 ቢሊየን ብር የሚሆነው ደግሞ ከሕብረተሰቡ ተሳትፎ የተገኘ ነው ብለዋል፡፡

ከተገነቡት ፕሮጀክቶች መካከል ጤና ጣቢዎች፣ መንገዶች፣ የኮሪደር ልማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ የገበያ ማዕከላት፣ ባሕላዊ ፍ/ቤቶች፣ ድልድዮች፣ የመጠጥ ውኃ ተቋማት እና ሌሎች ይገኙበታል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሥራ ሒደት ላይ ያሉ በርካታ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እንዳሉ ጠቁመው÷ በፍጥነት አጠናቅቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.