Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀኖይ በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቬትናም ሀኖይ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት ጀመረ።

የበረራ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ አዲሱ የበረራ አገልግሎት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከዓለም ለማስተሳሰር ያለውን ራዕይ ከመደገፍ ባሻገር ከደቡብ እስያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር የሚያግዝ ነው።

ለአየር መንገዱ ወደ ቬትናም የመጀመሪያው የመንገደኞች በረራው ሲሆን ሀኖይን ከአፍሪካ ጋር በንግድ እና ቱሪዝም ያላቸውን ትስስር እንደሚያጠናክር ተገልጿል።

በኤፍሬም ምትኩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.