Fana: At a Speed of Life!

  ተጠባቂው ፋና 80 የዳንስ ውድድር ፍጻሜ በመጪው እሁድ ይካሄዳል 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ላለፉት 9 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የፋና 80 ምዕራፍ 3 የዳንስ ውድድር በመጪው እሁድ ፍፃሜውን ያገኛል፡፡

በውድድሩ 16 የዘመናዊና የባህላዊ ዳንስ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን አራቱ እሁድ ለሚካሄደው የፍጻሜ ውድድር አልፈዋል።

ለፍፃሜ የደረሱት ጊዮን፣ ነገስታት፣ ጥያቄ ዘመናዊ የዳንስ ቡድን እና ኢትዮጵያ የባህል ቡድን ሲሆኑ፤ በደመቀ ሁኔታ በሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር ላይ በሁለት ዙር ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

በዕለቱ ኬሮግራፈር እና ከያኒ አዲሱ ደምሴ በክብር ዳኝነት ይገኛል።

የምዕራፉ የፍፃሜ ውድድር ተፋላሚዎች ለደረጃና ለገንዘብ ሽልማት ፉክክር የሚያደርጉ ሲሆን እንደየ ደረጃቸውም ከ200 ሺህ እስከ 70 ሺህ ብር ተሸላሚ ይሆናሉ።

አራቱም ቡድኖች በቀጣይ በሚካሄደው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ይሳተፋሉ።

እሁድ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሁለቱም የቴሌቭዥን አማራጮች ከፋና ቀለማት በኋላ የፍፃሜ ውድድሩን ይከታተሉ።

በሲሳይ ገ/ማርያም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.