አንድሬ ኦናና ከቅድመ ውድድር ዘመን ጨዋታዎች ውጪ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በጉዳት ምክንያት ከቅድመ ውድድር ዘመን ጨዋታዎች ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
የ29 ዓመቱ ካሜሮናዊ ግብ ጠባቂ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከስድስት አስከ ስምንት ሳምንታት ድረስ ከሜዳ እንደሚርቅ ተዘግቧል፡፡
የኦናናን ጉዳት ተከትሎ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ሌላ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ሊገደዱ እንደሚችሉ ቴሌግራፍ አስነብቧል፡፡
ኦናና በፈረንጆቹ 2023 ከኢንተር ሚላን ማንቼስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለበት ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ በሚሰራቸው ስህተቶች ትችት ሲያስተናግድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ በዚህ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት አርጀንቲናዊውን ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ጨምሮ ከተለያዩ ግብ ጠባቂዎች ጋር ስሙ በስፋት ሲነሳ ቆይቷል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ