Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል የ2018 በጀት 32 ነጥብ 823 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የክልሉን የ2018 ዕቅድ ማስፈፀሚያ በጀት 32 ነጥብ 823 ቢሊየን ብር በማድረግ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ምርጫ ዘመን 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ውሎው የ2018 በጀት 32 ነጥብ 823 ቢሊየን ብር እንዲሆን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።
በጀቱ በክልሉ ምክር ቤት የፋይናንስና በጀት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ጊንቦና የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ ከበደ ከንባታ አማካኝነት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ነው የፀደቀው።
አቶ ከበደ በዚህ ወቅት፥ የበጀቱ ምንጭ ከክልሉ ከውስጥ ገቢ፣ ከፌደራል መንግስት ከሚሰጥ ድጎማ እና ከሌሎች የገቢ ምንጮች እንደሆነ መግለጻቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የዲጂታል ቴክኖሎጂና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.