በጋምቤላ ክልል ከ15 ሚሊየን በላይ ችግኞች ይተከላሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ15 ሚሊየን በላይ ችግኞች ይተከላሉ።
የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር ቻም ኡሪየሚ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 15 ሚሊየን 900 ሺህ 65 ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል።
ከ16 ሚሊየን 97 ሺህ በላይ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ገልጸው÷ እስካሁን ከ8 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ጠቁመዋል።
በተከላ መርሐ ግብሩ የመንግስት እና የግል ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ብለዋል።
በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶችም በችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በንቃት እየተሳተፉ መሆናቸውንም አንስተዋል።
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!