Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 3ኛ አመት 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በሶስት አመታት ውስጥ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል።

ከ3 አመት በፊት የተረከብነውን ኃላፊነት በተገቢው ሁኔታ እየተወጣን ነው ያሉ ሲሆን፥ በርካታ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘታቸውን አንስተዋል፡፡

በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ህዝበ ሙስሊሙ መሪውን የሚመርጥበትን ምርጫ ሂደት በመገምገም ቀጣይ የስራ ዘመንን በተመለከተ ውሳኔ ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በሰዓዳ ጌታቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.