ትኩረት የሳበው የሆንግ ኮንግ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ሙዚየም
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሆንግ ኮንግ የተከፈተው የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሙዚየም በዓለም ዙሪያ ያሉ አድናቂዋቹን ትኩረት ስቧል፡፡
ሙዚየሙ የክርስቲያኖ ሮናልዶን የሁለት አስርት ዓመታት ድንቅ የእግር ኳስ ህይወት ጊዜያትን በተንቀሳቃሽ ምስል እና በፎቶ ያሳያል።
በትናንትናው ዕለት የወጡ ምስሎች እንደሚያሳዩት ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከልጅነት ክለቡ ስፖርቲንግ ሊዝበን ጀምሮ አሁን እስካለበት አልናስር የለበሳቸው ማልያዎች ይታያሉ፡፡
ሮናልዶ ከሀገሩ ፖርቹጋል፣ ከማንቼስተር ዩናይትድ፣ ከሪያል ማድሪድ እና ከጁቬንቱስ ጋር ያሳካቸው ዋንጫዎች እና የግል ሽልማቶች በሙዚየሙ ውስጥ በምስል እና በተንቀሳቃሽ ምስል ለእይታ ቀርበዋል።
ከሆንግ ኮንግ አስቀድሞ ሳዑዲ አረቢያ በሪያድ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ሙዚየም መስራቷ ይታወቃል፡፡
ሪያድ የሚገኘው በክርስቲያኖ ሮናልዶ ስም የተሰራው ሙዚየም ተጫዋቹ በእግር ኳስ ህይወቱ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች በሙሉ ያሳያል።
የ40 ዓመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሁን ላይ የዓለማችን ቁጥር አንድ ውዱ ተከፋይ ስፖርተኛ ሲሆን፤ በእግር ኳስ ሕይወቱ እስካሁን 938 ግቦች አስቆጥሯል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!