Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ የተመረቁ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች በታማኝነት የማገልገልና የትጋት ውጤቶች ናቸው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ የተመረቁ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች በታማኝነት የማገልገልና የትጋት ውጤቶች ናቸው አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ ከ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግልሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት÷ዛሬ የመረቅናቸው 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች በታማኝነት የማገልገል እና የትጋት ውጤቶች ናቸው ብለዋል፡፡

በተከናወነው ሥራ በእርጅና ብዛት የተጎሳቀሉና ለመማር ማስተማሩ ሒደት እንቅፋት የፈጠሩ እንዲሁም በሒደት በተማሪዎች የ12ኛ ክፍል አጠቃላይ ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የፈጠሩና የትምህት ጥራት ያጓደሉ ችግሮችን መቅረፍ መቻሉን አንስተዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በአጭር ጊዜ 6ኛ እና 8ኛ ክፍልን ጨምሮ በ2ኛ ደረጃ የተማሪዎች አበረታች ውጤት አስመዝግበናል ነው ያሉት ከንቲባዋ።

የተሻሻሉ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ ሙከራ፣ የሕፃናት ማረፊያ፣ ጽዱና አረንጓዴ ቅጥር ጊቢ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ያላቸውን የትምህርት መሰረተ ልማቶች እየተስፋፉ እንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡

የተቀናጀና የተናበበ እቅድ በመንደፍ የሥራ ባህላችንን በማሻሻል በሰራናቸው ስራዎች ውጤታማ ሆነናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የትምህርት ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና የት/ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል በያዘው እቅድ ባለፉት አምስት ዓመታት 110 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል ብለዋል።

በነባር ት/ቤቶች ውስጥ የማስፋፋያ ሥራ በመስራትም ከ30 ሺህ በላይ የመማሪያ ክፍሎችን፣ 334 መመገቢያ አዳራሾችን፣ 206 ቤተ ሙከራ እና ቤተ መጽሐፍት እንዲሁም የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መገንባቱን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም ትምህርት ቤቶች አካታች፣ ምቹ፣ ውብና ንፁህ፣ የደህንነትና የውበት ደረጃን የጠበቀ አጥር መገንባት መቻሉን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

ትውልድን መገንባት ቀዳሚው ሥራችን ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷በተከናወነው ሥራ በመሳተፍ ትውልዱ ላይ መልካም ዘርን ለዘሩ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.