Fana: At a Speed of Life!

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ፣ ሦስተኛ ዲግሪ እና በስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 590 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

በምረቃ ስነስርዓቱ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) እና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በመማር ማስተማር 70 ዓመታትን ያስቆጠረው በዩኒቨርሲቲው የትናንት ታሪክ፣ የዛሬ ስኬት፣ የነገ ተስፋ የሚስተጋበሩበት ነው።

ተመራቂዎች በተማሩበት የሙያ ዘርፍ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በትጋት በትብብር ማገልገል እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

እስከአሁን ከ107 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስመረቀው ዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ምሩቃንን ለማሰብም የቀድሞ ምሩቃን ቀንን እያከበረ ይገኛል።

በጳውሎስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.