Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ51 ሺህ በላይ የሚሆኑ የፍርድ ሂደቶች በኦንላይን ተካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ከተካሄዱ የፍርድ ሂደቶች መካከል ከ51 ሺህ በላይ የሚሆኑት የፍርድ ሂደቶች በኦንላይን ተካሂደዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ 6ኛው ጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የክልሉን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛል።

የፍርድ ቤቶችን የስራ አፈፃፀም አስመልክቶ እንደተናገሩት፤ በክልሉ በሶስቱም ደረጃ ባሉ ፍርድ ቤቶች በዓመቱ 548 ሺህ 744 ጉዳዮች ቀርበው 532 ሺህ 724 ጉዳዮች እልባት አግኝተዋል።

ከእነዚህ መካከል 51 ሺህ 911 ጉዳዮች በቪዲዮ ኮንፍረንስ የተካሄዱ ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ከተገልጋዩ 976 ሚሊየን 332 ሺህ ብር ወጪ ለማዳን ማስቻሉንም አንስተዋል።

በእንቅስቃሴ ላይ ከነበሩ አጠቃላይ ጉዳዮች 761 ሚሊየን 945 ሺህ 543 ብር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።

በፍርድ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ የዲጂታል መንገድን በመጠቀም ፈጣንና ግልፅ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ለመሆኑ አመላካች እንደሆነም ገልጸዋል።

ወደ ፍርድ ቤቶች የሚመጡ ጉዳዮች ከቀደመው በጀት አንጻር በ37 ሺህ 573 ጉዳዮች መቀነሱን ጠቅሰው፤ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት የመደበኛ ፍርድ ቤቶችን ጫና እያቃለለ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በባህላዊ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ሲታዩ ከነበሩ 482 ሺህ 556 ጉዳዮች መሀከል 443 ሺህ 686 ጉዳዮች ውሳኔ ማግኘታቸውን ጠቅሰው፤ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አስተዋእጾ እያደረጉ እንደሆነ አመልክተዋል።

በታምራት ደለሊ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.