በለንደን ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር አትሌት መዲና ኢሳ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በለንደን ዳይመንድ ሊግ የ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ አሸንፋለች፡፡
መዲና 5 ሺህ ሜትሩን በ14 ዲቂቃ ከ30 ሰኮንድ ከ57 ማይክሮ ሰኮንድ በማጠናቀቅ ነው ውድድሩን ያሸነፈችው፡፡
ሌላኛዋ አትሌት ፋንታየ በላይነህ በ33 ማይክሮ ሰኮንዶች ዘግይታ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ ፎትየን ተስፋይ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች፡፡