የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 በጀት 53 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ ፀደቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የቀረበውን 53 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ የክልሉን የ2018 በጀት አጸደቀ።
በጀቱ ከመደበኛ የመሥሪያ ቤቶችና ማዘጋጃ ቤቶች የውስጥ ገቢ እንዲሁም ከፌዴራል ድጎማና እርዳታ የሚሸፈን መሆኑ ተመላክቷል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በጀቱ በዋናነት ድህነት ቀናሽ በሆኑ የልማት ተግባራት እንዲሁም ለደመወዝና አስተዳደራዊ ጉዳዮች እንዲሚውል አብራርተዋል።
ከበጀቱ 65 በመቶ የሚሆነው የመሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብና የተጀመሩ የመንገድ፣ የውሃ፣ የጤና፣ የግብርና እና ትምህርት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እንዲሁም ለካሪኩለም ዝግጅቶችና የመጽሐፍ ህትመት ተደራሽ ለማድረግ ይውላል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የከተሞች መሠረተ ልማት አቅርቦት ለማጠናከር፣ ለዜጎች የስራ እድል ፈጠራ እና ነባር ፕሮጀክቶችን ለማስቀጠል የሚውል መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ከፈጣን ኢኮኖሚያዊ ልማት ባሻገር ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የማህበራዊ አገልግሎቶች ተደራሽነትና ጥራት ማሳደግም ሌላው የበጀቱ ትኩረት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በጀቱ ሕዝብን ሊጠቅሙ በሚችሉ የመሠረተ ልማቶችና ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ድልድል እንዲደረግ አሳስበዋል።
በማስተዋል አሰፋ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!