በክልሉ ፍርድ ቤቶች በተደረጉ ክርክሮች ከ251 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ተቻለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት በፍርድ ቤቶች በተደረጉ ክርክሮች ከ251 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሕዝብና መንግስት ሀብት ማዳን ተችሏል።
የክልሉ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ እሸቱ ጎዴቶ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በበጀት ዓመቱ የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም ከማስጠበቅ አኳያ ቢሮው ከሳሽ እና መልስ ሰጪ በመሆን በ1 ሺህ 7 የፍትሐብሔር መዝገቦች ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ተከራክሯል።
ክስና ክርክር ከተደረጉባቸው መዝገቦች መካከል በ824 መዝገቦች ላይ ውሳኔ መሰጠቱን ጠቅሰው÷ በ731 መዝገቦች ለመንግስት መወሰኑን አስረድተዋል።
በዚህም 251 ሚሊየን 555 ሺህ 501 ብር የሕዝብና የመንግስት ገንዘብ ለማዳን ተችሏል ነው ያሉት፡፡
በተጨማሪም በዓይነት 28 ሺህ 391 ካሬ ሜትር የከተማ መሬት እና 287 ሄክታር የገጠር መሬት በማዳን የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም ማስጠበቅ መቻሉን ተናግረዋል።
በተቃራኒ በተደረጉ ክርክሮች በ93 መዝገብ በመንግስት ላይ መወሰኑን ገልጸው÷ ከዚህ ውስጥ በ45 መዝገቦች ላይ ቀጣይ ክርክር ቢደረግባቸው አዋጭ አለመሆናቸውን በመገምገም እንዲዘጉ መደረጋቸውን አብራርተዋል።
በ48 መዝገቦች ላይ ደግሞ ይግባኝ ተጠይቆባቸዋል ነው ያሉት፡፡
በፍትሐብሄር ጉዳዮች በፍርድ ቤቶች የመርታት አቅምን 85 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ 90 ነጥብ 5 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል፡፡
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!