Fana: At a Speed of Life!

በፓርኮች ላይ በተሰራ የጥበቃና ልማት ሥራ አበረታች ለውጥ እየተመዘገበ ነው – ሰላማዊት ካሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በፓርኮች ላይ በተከናወነ የጥበቃና ልማት ሥራ አበረታች ለውጥ እየተመዘገበ ነው አሉ።

ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የሚሰጡ ሬንጀሮችን ለማሠብ ዓለም አቀፍ የሬንጀሮች ቀን በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተከብሯል።

ሰላማዊት ካሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ብሔራዊ ፓርኮችና በውስጣቸው የሚገኙ የዱር እንስሳትና ዕፅዋት ጥበቃን ይበልጥ በማጠናከር ለቱሪዝም መስህብ እንዲውሉ በትኩረት እየተሰራ ነው።

በፓርኮች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ጉዳዮችን በመከላከል የጥበቃውንና የልማቱን ሥራ በማጠናከር በተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ለውጦች እየተመዘገቡ ነው ብለዋል።

በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከበረው ዓለም አቀፍ የሬንጀሮች ቀን የዚሁ ጥረት አካልና በዘርፉ የተጎዱ ሬርንጀሮችን ለማስታወስ ያለመ እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ በበኩላቸው÷ብሔራዊ ፓርኮችን ከሰው ሰራሽና ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

በተለይ ሕገ-ወጥ ሰፈራ፣ አደንና ሰደድ እሳት በፓርኮቹ ላይ ጉዳት በማድረስ ትልቁን ድርሻ የሚይዙ ተግዳሮቶችን ለመከላከል ከአካባቢው ማህበረሰብና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ለፓርኮችና የተፈጥሮ ኃብት የምታደርገው እንክብካቤ የሚደነቅ እንደሆነ ያወሱት ደግሞ የዓለም አቀፍ የሬንጀሮች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ክርስቶፈር ጁሊያርስ ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.