Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ880 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ1 ነጥብ 55 ቢሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ታቅዶ አስካሁን ከ880 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ።

በቢሮው የተፈጥሮ ሐብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለአለም ምህረቱ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት፥ እስካሁን 114 ሺህ ሄክታር መሬት በችግኝ ተሸፍኗል።

ይህም የዕቅዱን 56 በመቶ እንደሆነ ጠቅሰው፥ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከተጀመረ ወዲህ በየቀኑ እስከ ሶስት ሚሊዮን ሰዎች አረንጓዴ አሻራቸውን እያስቀመጡ ነው ብለዋል።

“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ የሚገኘው የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በተያዘለት እቅድ መሰረት እየተካሄደ መሆኑንም ነው የገለጹት።

ቢሮው በመጪው ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም የዘንድሮውን የችግኝ መርሐ ግብር ሙሉ ለሙሉ ተክሎ የማጠናቀቅ ግብ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም ነው ያብራሩት።

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.