Fana: At a Speed of Life!

በአዳባ ወረዳ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ልዩ ስሙ ጋራ ወሻ በተባለ አከባቢ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ 10 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

የወረዳው የትራፊክ ደህንነት ኃላፊ ኢንስፔክተር ሀሽም ኢልሚ ለፋና ዲጅታል እንዳሉት፥ በአደጋው ከሟቾች በተጨማሪ በ6 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በተለምዶ ዶልፊን ተብሎ የሚጠራው የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ 16 ሰዎችን ጭኖ ከባሌ ዞን ዲንሾ ወረዳ ወደ አዳባ ወረዳ ሲጓዝ በነበረበት ወቅት የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበት ተናግረዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ ከፍጥንት በላይ ማሽከርከር መሆኑንም ነው ኃላፊው የገለጹት፡፡

በዮናታን ብርሃኑ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.