Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምግብ ሥርዓቶች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ከተገኙ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር በመሆን ችግኝ በመትከል አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በኢትዮጵያ እና ጣሊያን የጋራ አዘጋጅነት የተሰናዳው 2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓቶች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ከተገኙት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር በመሆን የአረንጓዴ ዐሻራችንን አሳርፈናል ብለዋል።

አክለውም ይኽ ተግባር ለፈተና የማይበገር እና ዘላቂ የምግብ ሥርዓት በመገንባት ሂደት የድነና እና የአካባቢ ጠባቂነትን ቀዳሚ ሚና የሚገልጽ እንደሆነ በመልዕክታቸው ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.