Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ኩባ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ኩባ በተለያዩ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ጎን ለጎን ከኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ኩባ ለ50 ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰው፤ ይህንንም ግንኙነት በተለያዩ የትብብር መስኮች ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል፡፡

በሁለትዮሽ ውይይቱ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ እንዲሁም በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ትብብርን ለማጠናከር መስማማታቸውን ጠቁመዋል።

የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ የምታከናውነውን የልማት እንቅስቃሴ በማድነቅ ባለፉት ዓመታት የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እየሰራች ያለው ስራ አበረታች ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ የሚታዩ ለውጦች በእጅጉ መደነቃቸውን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.