Fana: At a Speed of Life!

ዦአው ፌሊክስ አልናስርን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሳዑዲው ክለብ አልናስር ፖርቹጋላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ዦአው ፌሊክስ ከቼልሲ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

የ25 ዓመቱ ተጫዋች በ30 ሚሊየን ዩሮ መነሻ የዝውውር ሂሳብ አልናስርን የተቀላቀለ ሲሆን፥ በሳዑዲ ፕሮ ሊጉ ክለብ እስከ ፈረንጆቹ 2027 የሚያቆየውን ውል ፈርሟል፡፡

ተጫዋቹ ከቼልሲ በተጨማሪ ለኤሲ ሚላን፣ ባርሴሎና፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ቤኔፊካ ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ከፊርማ ስነ ስርዓቱ በኋላ በሰጠው አስተያየት እዚህ የመጣሁት ደስታን ለመፍጠር ነው አብረን እናሸንፋለን ሲል ተናግሯል፡፡

ዦአው ፌሊክስ በአልናስር ቆይታው ከብሄራዊ ቡድን አጋሩ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር በጋራ ይጫወታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.