የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለግሉ ዘርፍ የ121 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ፈቀደ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግሉ ዘርፍ ካቀረባቸው የውጭ ምንዛሪ ጥያቄዎች ውስጥ 505 ያህሉን በማጽደቅ የ121 ሚሊየን ዶላር ፈቅጃለሁ አለ፡፡
ባንኩ ከቀረቡለት ጥያቄዎች ውስጥ 81 በመቶ ለሚሆኑት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ አይነቶችን ለተለያዩ ፍላጎቶች መፍቀዱን ገልጿል።
ይህ ወሳኝ ፈቃድ ባንኩ እንደ ማዳበሪያ፣ ነዳጅ እና ሌሎች የገቢና የአገልግሎት ክፍያ ፍላጎቶች በየቀኑና በመደበኛነት ከሚያደርገው የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ተጨማሪ ነው ብሏል።
የውጭ ምንዛሪ ፈቃድን ከደንበኞቹ ፍላጎትና ከሀገሪቱ ስትራቴጂካዊ ቅድሚያዎች ጋር በማጣጣም በመደበኛነት ምላሽ እንደሚሰጥ ባንኩ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡