Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ሲቲ ጀምስ ትራፎርድን አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ሲቲ እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ ጀምስ ትራፎርድን ከበርንሊ ማስፈረሙን ይፋ አደርጓል፡፡

የ22 ዓመቱ ግብ ጠባቂ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከበርንሊ ጋር በሻምፒዮንሺፑ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ክለቡ ከአንድ ዓመት የሻምፒዮንሺፕ ቆይታ በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ቢመለስም ግብ ጠባቂውን ለማንቼስተር ሲቲ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡

ግብ ጠባቂው በ2024/25 የውድድር ዓመት በሻምፒዮንሺፑ ለበርንሌይ 45 ጨዋታዎች ላይ ግልጋሎት መስጠት ችሏል፡፡

እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ በማንቼስተር ሲቲ ቤት 1 ቁጥር ማሊያን እንደሚለብስ ተረጋግጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.