Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የቱሪዝም ዘርፉን የስበት አቅም ያሳድጋል – ሰላማዊት ካሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የቱሪዝም ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል አሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፡፡

ሰላማዊት ካሳ በሸገር ከተማ አስተዳደር ኩራ ጂዳ ክ/ከተማ በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ችግኝ ተክለዋል፡፡

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እየተከናወነ ያለው ሥራ የቱሪዝም ዘርፉን የስበት አቅም የሚጨምር ነው፡፡

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከለውጡ ሒደት ጅማሮ ወዲህ እየተሰሩ ከሚገኙ ለትውልድ ከሚተርፉ በርካታ ኢኒሼቲቮች መካከል ተጠቃሽ መሆኑን አውስተዋል፡፡

መርሐ ግብሩ የተራቆቱ አከባቢዎች መልሰው የሚለሙበት እና መዳረሻዎችም ውበት የሚጎናፀፉበት በመሆኑ ለቱሪዝም ዘርፉ ልማት ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡

በታምራት ደለሊ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.